በግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይልና በትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ መሃል መገንባት የጀመረውን ወገናዊ ትስስር የሚያሳይ የቪድዮና የዜማ ቅንብር

Home » Video » በግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይልና በትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ መሃል መገንባት የጀመረውን ወገናዊ ትስስር የሚያሳይ የቪድዮና የዜማ ቅንብር

Sep 20, 13 • by

በዚህ የመዝሙር ቪድዮ የሚሰማው ዜማና ድምጽ፣ እንዲሁም የሚታየው የድምጻውያን ምስል የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (የትህዴን) ነው። የቪድዮ ቅንብሩ የተዘጋጀው በትህዴን የህዝብ ግንኙነት ክፍል ነው። በቪድዮ የሚታየው የሰራዊት ምስል ከግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል የሶስተኛ ዙር ሰልጣኖች የምረቃ በአል ላይ የተወሰደ ነው።

የትህዴን የባህል ክፍል ይህን ዜማ  የደረሰውና  የተጫወተው ለግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል ያለውን የወገንተኛነትና የአንድነት ስሜት ለመግለጽ ነው።

ግንቦተ\ት 7 ህዝባዊ ሃይል ከተመሰረተበት እለት አንስቶ ከትህዴን አመራርና አባላት በተለገሰው ወገናዊ ፍቅርና ድጋፍ፣ በተመለከተው የትህዴን አባላት ኢትዮጵያዊ ስሜትና ጀግንነት ኮርቷል።

የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል ከትህዴን ጋር የጀመረው  ወገናዊ ትስስር፣ የወያኔን አምባገነናዊና ከፋፋይ ስርአት ከሃገራች ምድር በመጥረግ፣ በቦታው የዜጎች አንድነት የሚጠብቅበትን፣ እኩልነትና  ፍትህ የሰፈነበተን፣ የሃገር ክብርና ጥቅም የሚጠበቅበትን የፖለቲካ ስርአት መሰረት በመጣል ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት እርግጠኞች ነን።

ዘላለማዊ ክብርና ሞገስ ለኢትዮጵያና ለህዝቧ ሲሉ ለዘመናት መስዋእነት ለከፈሉት ልጆቿ  በሙሉ !!!

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ነጻነትና ክብር ሲሉ የመጨረሻውን መስዋእትነት ለመክፈል ለቆረጡ ልጆቿ በሙሉ !!!

የግንቦት7 ህዝባዊ ሃይል ህዝብ ግንኙነት

Pin It

« »

Scroll to top